በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት በተከሰቱ እሳት አደጋዎች ከ200 ሺህ በላይ ብር ሲወድም ከ6 ሚሊዮን በላይ ብር ግምት ያላቸው ንብረተቶችን ደግሞ መታደግ ተገለጸ።

ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ ሁለት ድንደገተኛ የእሳት አደጋ መከሰታቸውን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

የመጀመርያ የእሳት አደጋ የደረሰው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ቡልጋሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መኖርያ ቤት ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በዚህ አደጋ ምክንያት 200 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ ሰራተኞች ከአደገው 3 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ማዳናቸውም ተገልጿል፡፡

ሁለተኛው የእሳት አደጋ የደረሰው ደግሞ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት በአንድ የእህል መጋዘን ቤት የድረሰ አደጋ ነው፡፡

በዚህኛው አደጋ ምክንያትም 10 ሺህ ብር የሚሆን ንብረት ለጉዳት እንደተዳረገ እና 3 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ከጉዳት ማዳን እንደተቻለ የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *