የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማጓጓዝ ከዓለም አቀፍ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ጋር በመምከር ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተመርቶ ወደ ገበያ መግባት ያልጀመረ ቢሆንም ምርቱ ሲጠናቀቅ ለመላው አለም በጥንቃቄ እና በፍጥነት ለማጓጓዝ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የአየር መንገዱ አለም አቀፍ በረራ አገልግሎት ዳሬክተር አቶ ለማ ያደቻ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ሀገራት የኮቪድ-19 ክትባትን በስፋት ለማምረት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ገልፀው ክትባቱ በሚደርስበት ወቅት ደግሞ ለመላው የአለም ሀገራት ማከፋፈል የራሱ የሆነ ጫና ይፈጥራል፡፡

ይህንን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ክትባቱን በስፋት ወደ ማምረት ሲገባ ጥንቃቄ በተሞላበትና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለአለም ሀገራት ለማሰራጨት በቂ ዝግጅት አድርገናል ብለዋል፡፡

አለምን ከኮቪድ ለመታደግ የሚሰራውን ክትባት ለማጓጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተመራጭ በመሆን አለምን እንደሚታደግ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዱ እስካሁን ለሙከራ እየተመረቱ የሚገኙትን ክትባቶች ከተለያዩ ሀገራት እያጓጓዘ ሲሆን ወደ ትልቅ ስምምነት ያልተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባት ማጓጓዝን በተመለከተ አለም ላይ ካሉ ትልልቅ የካርጎ አንቀሳቃሾች ጋር በጋራ እየሰራን ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከእነርሱ ጋር የጠበቀ የስራ ውል እንዳለውም አብራርተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *