አስቸኳይ ጉዞ ላላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መታወቂያ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ አዲስ መታወቂያ ማውጣት፣ማደስ እና መሸኛ መስጠት መታገዱ ይታወሳል።

ይህ እገዳ የሚቀጥለው አሁን ያለው ሃገራዊ ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

በቀጣይ የተሻለ መፍትሄ እስኪገኝ ደረስ አሁን ባለው ሁኔታ እንደሚቀጥል የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

ይሁንና ለአስቸኳይ ሁኔታ እንደ ህክምና፣ የውጪ ሃገር ጉዞ፣ለትምህርት እና መሰል ሁኔታዎች ላላቸው እና ለነዚህ ማስረጃ ማቅረብ ለሚችሉ ዜጎች አገልግሎቱ ይሰጣል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *