በአዲስ አበባ አድዋ ድልድይ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ቦንብ ፈንድቶ በአንድ ግለሰብ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አድዋ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአንድ ግለሰብ ላይ ቀላል ጉዳት እንደደረሰ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በደረሰበት ጉዳት በምኒልክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ግለሰብ የታክሲ ረዳት ሲሆን ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ እንደገባና በማዳበሪያ የተጠቀለለ እቃ ተመልክቶ በእግሩ ሲረግጠው ከዚያ በኋላ ራሱን እንደሳተ ተናግሯል፡፡

የህገ-ወጡ ህወሓት ቡድን ተላላኪዎች በከተማችን የጥፋት ተግባር ለመፈፀም ያዘጋጇቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ ሀይሉ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውሶ የፀጥታ ኃይሉ ጠንከራ እንቅስቃሴ እና ሕብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን እያደረገ ያለው ክትትል ያስጨነቃቸው የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች በህዝቡ ላይ ጉዳት ለማድረስ በማቀድ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችን በመጣል ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ባለማወቅ ራሱን ለአደጋ እንዳያጋልጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

እስካሁን ለተገኘው ውጤት የህብረተሰቡ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆ በህገወጥ ቡድኑ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *