የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የሌሎች የክልሉ ባለስልጣናትን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

ምክር ቤቱ የዶ/ር ደብረጸዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የሌሎችን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በዚህም መሰረት፦

ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
አቶ አባይ ፀሃዬ
ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
አቶ ጌታቸው ረዳ
አቶ አፅበሃ አረጋዊ

አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም ላይ የቀረበው ያለመከሰስ መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው መሆኑ ታውቋል።

የፌደሬሽን ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት የትግራይ ክልል መንግስት እንዲፈርስ እና በምትኩ ጊዜያዊ አስተዳድር እንዲቋቋም መወሰኑ ይታወቃል።

ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የምዕራብ ትግራይ ሙሉ ለሙሉ በአገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *