የጌድዮ ዞን 50 ሺህ ሊትር ቤንዚል ነዳጅ እንደተሰወረበት አስታወቀ።

የኢትዮጵያን የነዳጅ ፍላጎት በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት አማካኝነት ከመካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች አገራት ነዳጅን ወደ ወደብ ያጓጉዛል።

በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የግል ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ደግሞ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ወዳሉ የነዳጅ ማደያዎች ያደርሳሉ።

በደቡብ ክልል ለጌዲዮ ዞን ነዳጅ የሚያቀርበው ዋስ የተባለ የግል ተቋም ሲሆን ይህ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት 50 ሺህ ሊትር ቤንዚል አልደረሰኝም ሲል ገልጿል።

ዋስ የተሰኘው ነዳጅ አቅራቢ ተቋም ከጅቡቲ ወደብ 50 ሺህ ሊትር ነዳጅ በጌድዮ ዞን ስም ያነሳ ቢሆንም ነዳጁ አልደረሰኝም ብሏል።

የጌዲያ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አቶ ወርቅነህ ጋሹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ክልሉ የትኛው ነዳጅ ማደያ ጥያቄ አቀረበ የሚሉና የትኛውስ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ከጅቡቲ ወደብ አነሳ የሚለውን በየ ቀኑ ይከታተላል፡፡

መረጃዎቹንም በየቀኑ ለዞኑ እንደሚልክ ያመለከቱት ሀላፊው በደረሰን መረጃ መሰረት የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት ክትትል እንደሚያርግ ጠቁመዋል፡፡

በዚህም መሰረት በዲላ ከተማ ዋስ የሚባል ነዳጅ አቅራቢ ተቋም ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ከጅቡቲ ወደብ 50 ሺህ ሊትር ቤንዚል ነዳጅ ያነሳ መሆኑን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ለዞኑ መረጃ አድርሷል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በወቅቱ ነዳጁ ወደ ዲላ ከተማ ያልገባ ሲሆን እስካሁን የት እንደደረሰ አይታወቅም፡፡

አቶ ወርቅነህ እንደሚሉት ምናልባትም ቤንዚሉ በጥቁር ገበያ ሳይሸጥ እንዳልቀረ ጥርጣሬያቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በዚህም ክልሉ ነዳጁ ከጅቡቲ ወደብ መነሳቱን ማረጋገጫ ልኮልናል ያሉት ሀላፊው በህጉ መሰረት በክልሉም በዞኑም ደረጃ በተቋሙ ላይ እርምጃ ይወስዳል በማለት ተናግረዋል፡፡

የተላኩት ሌሎች ማደያዎች የተፈቀደላቸውን መጠን ማምጣታቸውን ገልፀው ዋስ የተባለው ማደያ ባለማምጣቱ አቅራቢው ላይ ክስ መመስረታቸውን ነግረውናል፡፡

አሁን አሁን በኢትዮጵያ የቤንዚል ነዳጅ ግብይት ወደ ጥቁር ገበያነት እየተቀየረ ነው የሚሉት አቶ ወርቅነህ መንግስት ከፍተኛ ድጎማ በማድረግ ወደ ሀገር ቤት የሚገባ በመሆኑ ከፍተኛ ቁጥጥር ያሸዋል በማለት ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ጎሮቤት ሀገራት ቤንዚል በከፍተኛ መጠን ውድ በመሆኑ አቅራቢዎች ወደ ጎሮቤት ሀገራትም የሚያሸሹበት ሁኔታም እንዳለ ተገንዝበናል ብለዋል፡፡

ችግሩ ያለው ቤንዚል በሚያቀርቡት ላይ ሲሆን ናፍጣን ጨምሮ ሌሎች የነዳጅ አይነቶች ላይ ምንም ችግር አልተፈጠረም፡፡ በከተማውም የቤንዚል እጥረቱ በከፍተኛ መጠን መጨመሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከዚህ ቀደም ግን እጥረቱን በተመለከተ ማህበረሰቡ መንግስትን ሲያማርር እንደነበር ገልፀው አሁን ግን እነዚህ ህገ-ወጥ አቅራቢዎች ላይ ቁጥጥር በማድረጋችን አቅርቦቱ እየተሻሻለ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ዋስ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትን አስተያየት ለማካተት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ትኩስ ዜናዎችን፣ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *