በኢትዮጵያ የፖሊዮ ወረርሽኝ የዘመቻ ክትባት ያልደረሳቸው ህጻናትን ነገና ከነገ ወዲያ እንዲከተቡ የፌደራል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።

ባሳለፍነው አርብ ተጀምሮ የነበረው የፖሊዮ ወረርሽኝ ክትባት እስከ ዛሬ ሰኞ ህዳር 7 ቀን እየተሰጠ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ያልደረሳቸው ህጻናት ካሉ ነገና ከነገ ወዲያ በተጨመረው ቀን ማስከተብ ይችላሉ ሲሉ የኢንስቲትዩቱ የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ መስፍን ወሰን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ደቡብ ሶማሌ ሀረሪ ክልሎችና በአዲስ አበባና ድሬድዋ ለ7 ሚሊየን ህጻናት ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ክትባቱ 90 በመቶ እንደተሳካም አቶ መስፍን ነግረውናል።

አፋርና አማራ ክልል 5 ዞኖች የፖሊዮ ወረርሽኝ ምልክት አንደታየ የተገለጸ ሲሆን የሀገሩ ወቅታዊ ሁኔታ ካመቸን በሚቀጥሉት ሳምንታት ክትባቱን ለመስጠት አቅደናል ሲሉ አቶ መስፍን ወሰን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ዜናዎችን፣ ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.