ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ተገለፀ፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ተገለፀ፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግ የአለም መንግስታትን በመጠየቅ እረገድ ሙሉ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ገልፀዋል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ለአናዶሉ ኤጀንሲ እንደተናገሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት በህወሀት ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ዶ/ር ቴውድሮስ ሲያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በህወሃት ላይ የሚወስደውን ወታደራዊ እርምጃ እንዲያስቆሙ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ሲጠይቁ ነበር ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2017 ጀምሮ በአለም ጤና ድርጅት (WHO) ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር ቴድሮስ የህወሀት ቡድን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2005 እስከ 2012 የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም ከ 2012 እስከ 2016 ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ዜናዎችን፣ ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ሕዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.