በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአነፍናፊ ውሾች ቤት ሊገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ ዱር እንስስት ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ወደ ውጪ አገር እንዳይወጡ ለመከላከል በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአነፍናፊ ውሾች ቤት ሊገነባ መሆኑን ገልጿል።

8 ሰዎች በህገ ወጥ የእንስሳት አካል ዝውውር ተግባር ላይ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ባለስልጣኑ ገልጿል።

የባለስልጣኑንን የሶስት ወራት ሪፖርት ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ 8 ሰዎች በህግ ወጥ የእንስሳት አካል ዝውውር ላይ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በነዚህ ተጠርጣሪ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት ውስጥም 400 ኪግ የሚመዝን የዝሆን ጥርስ መገኘቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የከርከሮና የአቦሸማኔ አካል መገኘቱም አቶ ኩመራ ገልጸዋል።

እንዲ ያሉ ወንጀሎችን ለመግታትና የኢትዮጵያ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ወደ ውጪ ሀገር እንዳይወጡ ለማድረግ የአነፍናፊ ውሻ ቤት በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱንም አቶ ኩመራ ተናግረዋል።

የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን በቋሚ የአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ለዩኔስኮ ጥያቄ ማቅረባቸውን እና ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ድንበር ተሻጋሪ ህገ ወጥ የእንስሳት ዝውውርን ለማስቀረት የኢጋድ አባል ሀገራት በኢትዮጵያ አነሳሽነት የስምምነት ፊርማ ተደርጓል።

ኢትዮጵያ ጅቡቲ ሱማሊያ፣ደቡብ ሱዳን፣ሱዳን እና ዩጋንዳ የስምምነቱ አካላት ናቸው የተባለ ሲሆን ኤርትራም በቅርቡ ትቀላቀላለች የሚል ሀሳብ እንዳላቸው አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *