አቢሲኒያ ባንክ በአዲስ አበባ ለዋና መስሪያ ቤቱ ባለ 60 ወለል ህንጻ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።

አቢሲኒያ ባንክ 24ኛው አመታዊ መደበኛ የባላክሲዮንች ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ባንኩ በዚህ ጊዜ እንዳስታወቀው ለዋና መስሪያ ቤት የሚያገለግል 9 ሺህ 763 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ባለ 60 ወለል ህንጻ ሊገነባ መሆኑን ገልጿል።

ባንኩ ደንበል ሕንጻ አካባቢ የነበሩት ሁለት ይዞታዎች ለኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ማስፋፊያ ግንባታ በማስረከቡ አዲሱ ህንጻ የሚገነባው በምትክነት በተሰጠው ቦታ ላይ መሆኑም ገልጿል ።

ህንጻው የሚገነባውም በአዲስ አበባ ልደታ ክፈለ ከተማ ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን የሚገኝ ቦታ ላይ መሆኑን አስታውቋል።

እስከ 60 ወለል የሚኖረው ህንጻ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ አለም አቀፍ ተቋራጮች የፍላጎት ማሳወቂያ ሰነድ ማቅረባቸውም ተነግሯል ።

ይህንን ተከትሎ ባንኩ የጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ሰምተናል።

አቢሲኒያ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 47 ነጥብ 63 ቢሊየን ብር መድረሱንም አስታውቋል።

በዳንኤል መላኩ
ሕዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *