የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የአየር ሰዓት ድልድል መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ቦርዱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የአየር ሰዓት ድልድል መመሪያ የተዘጋጀ ሲሆን በነገው ዕለት በዚህ መመሪያ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ተቋማት እና ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ ይመክራል።

ምርጫ ቦርዱ፣በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 የተሰጡትን ሃላፊነቶችና ግዴታዎች ለመወጣት እንዲያስችለዉ የተለያዩ መመሪያዎችን እያረቀቀ እንደሚገኝም ገልጧል፡፡

ከነዚህ መመሪያዎች መካከልም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀምና ድልድል መመሪያ ይገኝበታል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ሕዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *