የሕወሃት ልዩ ሃይል ያፈረሳቸው ድልድዮችን በፍጥነት ገንብቶ ለአገልግሎት እንደሚያበቃ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ላይ ሆን ተብለው በልዩ ሃይሉ የፈረሱ ድልድዮችን መልሶ በመገንብት ለህብረተሰቡ ጥቅም እንዲውሉ አደርጋለሁ ብሏል።

እነዚህ ድልድዮችን እና መንገዶችን በጊዜያዊነት ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው ለመመለስ የብረት ድልድይ መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

አሁን ላይ በጦርነቱ ተጎድተው የማያሳልፉ መንገዶች የአስፋልትም ይሁን የጠጠር መንገዶችን እንደሚጠግኗቸውም ተናግረዋል፡፡

የተጎዱ መንገዶችን በሚመለከት የተሟላ መረጃ አለን፣ የት የት ቦታ ችግር እንደገጠመ እና ያንን መልሶ ወደ ስራ ለዐማስገባት ዲስትሪክቶችም ዝግጁ ናቸው ፣ ችግሩ ስጋት ሆኖ እንደማይቀጥልም ኢንጅነር ሃብታሙ ገልጸዋል፡፡

ኢንጅነር ሃብታሙ በፌዴራል መንግስት የሚሰሩ እንዳሉ ሁሉ በክልል መንግስትም የሚሰሩ እና የሚጠገኑ መንገዶች መኖራቸውን እና ክልሎች የሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ካለ እናግዛቸዋለን ብለዋል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሕዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.