የቡድን 20 አባል ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባትን ለሁሉም የአለም ሀገራት ለማድረስ 21 ቢሊዮን ዶላር መደቡ፡፡

የቡድን 20 አባል ሀገራት መሪወች በሳውዲ አረቢያ በነበራቸው የቪርቹዋል ስብሰባ ላይ እንዳሉት፤ የኮቪድ 19 ቫይረስ ክትባት፣ መከላከያና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለሁሉም የአለም ሀገራት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ መስማማታቸው ተሰምቷል፡፡

መሪዎቹ በተለይ በኤዥያና በአፍሪካ አህጉር ላሉ ሀገራት ክትባቱን በተቀላጠፈና በበቂ መጠን እንዲሁም ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ቶሎ እንዲደርስ የሚያስችሉ ቅድሚያ ስራዎች በሙሉ መጠናቀቃቸውን በስብሰባው ላይ ተናግረዋል፡፡

ይሄው የኮሮና ቫይረስ እንደወረርሽኝ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን በአለም ላይ ከ58 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በበሽታ አጥቅቷል፤ 1.3 ሚሊዮን ሰዎችን ደግሞ ለህልፈተ ህይወት መዳረጉም ይታወሳል፡፡

እንዲሁም በአለም ላይ 11 ትሪሊዮን ዶላር ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራን እንዳስከተለ ይነገራል፡፡

ስለሆነም የቡድን 20 አባል ሀገራት ለኮሮና ቫይረስ ክትባት ማምረቻና ማጓጓዣ የሚዉል 21 ቢሊዮን ዶላር መድበው፤ ክትባቱ ከተመረተ በኋላም ለሁሉም ሰዎች እኩል ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛሉ ሲል አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በጅብሪል ሙሃመድ
ሕዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *