ሎዛ አበራ በቢቢሲ የዓለማችን 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ውስጥ ተካተተች።


ቢቢሲ ለ2020 በዓለም ዙሪያ 100 ተፅኖ ፈጣሪ ያላቸውን ሴቶች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

ታዲያ በዚህ ውስጥ ኢትዮጲያዊቷ እግር ኳስ ተጫዋቿ ሎዛ አበራ ተካታላች፡፡

ከነዚህ ተፅእኖ ፈጣሪ ሴቶችም በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ለማህበረሱ ለውጥ ያመጡ መሆናቸውን ቢቢሲ አስቀምጣል፡፡

ዝርዝሩ የፊንላንዳ ሳና ማሪን ፣ የአዲሱ የአቫተር እና የማርቬል ፊልሞች ኮከብቧ ሚሸል ዮህ እና የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲዋ ተመራማሪ በኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እየበረከተች ያችው ሳራ ጊልበርት ይገኙበታል፡፡

እንዲሁም የማንችስትር ዩናይትዱ የፊት መስመር አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ አነሳሽነት የተጀመረው ለችግር ተጋላጭ ህጻናትን የመመገብ መርሃ ግብር አቀንቃኝ የሆነችው እና ኢትዮጵያዊ የዘር ግንድ እንዳላት የምትጠቀሰው ክርስቲና አዳነም በዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ውስጥ ተካታለች።

በየውልሰው ገዝሙ
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *