የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል የፌደራል መንግስት የሰጠውን የ72 ሰዓት በመጠቀም እጅ እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካት የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ ነው።

በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ ነው።

ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ፣ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ፣ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት ማሳሰቡን በመግለጫው ገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *