ትናንት ምሽት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የተሰበሰበው የጸጥታው ምክር ቤት ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ።

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ትግራይ ዉስጥ ሥለሚደረገዉ ዉጊያ ትናንት ሌሊት በመንግስታቱ ድርጅት ዋና መቀመጫ ኒዮርክ ተሰብስቦ ነበር።

ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ቀደም ሲል ይዞት ለነበረዉ ቀጠሮ የአፍሪቃ ሐገራት ድጋፍ ባለመስጠታቸው ምክንያት ሰርዞት ነበር።

ይሁንና በምክር ቤቱ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉን ፈረንሳይና ብሪታንያን፣ ጨምሮ የአዉሮጳ ሐገራት ዉይይቱ እንዲደረረግ ግፊት በማድረጋቸዉ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ዙሪያ መሰብሰባቸው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ሶስተኛ ሳምንቱን የያዘዉ ጦርነት በርዕስነት እንዲቀርብ ከፈረንሳይና ከብሪታንያ በተጨማሪ ግፊት ያደረጉት ቤልጂየም፣ ጀርመንና የወቅቱ የጸጥታው ምክርቤት ተለዋጭ አባል የሆነችው ኢስቶኒያ ናቸዉ።

አፍሪካን ወክለው የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል የሆኑት ደቡብ አፍሪካ፣ኑጀር እና ቱኒዝያ የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት ጦርና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታጣቂዎች ሥለገጠሙት ጦርነት መረጃ የሚያሰባስብ የመልዕክተኞች ጓድ ወደ ኢትዮጵያ መሔድ አለበት በሚል ምክንያት ጉዳዩ ለዉይይት መቅረቡን ተቃውመው ነበር።

ይሁንና በመጨረሻም ስብሰባው ያለ ስምምነት መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጦርነቱ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው የትኛውም አገር በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ አሳስበዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *