በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ፈነዳ።

ኮሚሽን እንዳስታወቀው የቦንብ ፍንዳታው ምንም ጉዳት አላደረሰም ብሏል፡፡

ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ከአካባቢው ሰዎች በደረሰው ጥቆማ የፈንጅ አምካኝ ባለሙያዎች ወደ ቦታው በማቅናት ለማምከን ባደረገው ሙከራ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሊፈነዳ ችሏል።

በዚህም አንድ ግለሰብ የቦንቡ ፍንጣሪ በቅርብ ርቀት ከሚሰራበት ጋራዥ ቅጥር ግቢ በስራ ላይ ሳለ በፍንጣሪው ቀላል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ተጎጂው የህክምና ርዳታ በማግኘት ወደ ቤቱ መመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እየገለፀ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦችና አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት እንደደረሰን የምናሳውቅ ሲሆን በተመሳሳይ በዚሁ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፖሊስ በደረሰ መረጃ መሰረት ባለሙያዎች ቦታው ድረስ በመገኘት ቦንቡን የማምከን ስራ ሰርተዋል፡፡

በነብስ ውጪ ግቢ ጣር ላይ የሚገኘው የጁንታው ተላላኪዎች በከተማችን አዲስ አበባ በንፁሃን ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ የሚደርጉትን መንፈራገጥ ለማምከን የሚቻለው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ በማጠናከርና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ መሆኑን ኮሚሽኑ ማስገንዘብ ይወዳል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *