ቦትስዋና በጥገኝነት አስጠልላቸው የነበሩ 10 ሺህ የአንጎላ ዝሆኖችን መለሰች።

ደቡብ አፍሪካዊቷ ቦትስዋና ከ130 ሺህ በላይ ዝሆኖችን በመያዘ በአለም እጅግ ብዙ ቁጥር ያለቸው ዝሆኖች የሚኖሩባት ሀገር መሆኗ ይነገራል፡፡

በዚህም ለዝሆኖችና ለሌሎች እንስሳት የተሟላ ግጦሽና የውሃ አቅርቦት ያላት በመሆኗ ለእንስሳቱ መሪቢያ ምቹ መሆኗም ይነገርላታል ቦትስዋና።

ዝሆኖቹ በአንጎላ እኤአ ከ1975 እስከ 2002 ውስጥ በነበረው የርስበርስ ጦርነት ምክንያት ሀገሪቷ ለጦርነቱ እንጂ ለእንስሳቱ ጥበቃና ደህንነት ጊዜ ባለመስጠቷ ዝሆኖቹ ለህገ ወጥ የዝሆን ጥርስ አዳኝ ሰወች ተጋላጭ እንደነበሩ ተገልጿል።

በዚህም የዝሆኖች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ያሳሰባት አንጎላ ለዝሆኖች ምቹ ወደሆነችው ጎረቤቷ ቦትስዋና 10 ሺህ የሚሆኑ ዝሆኖችን በጥገኝነት እንዲኖሩ ማድረጓ ተነግሯል።

ከሰሞኑ ታዲያ እኤአ ከ 2002 ጀምሮ በቦትስዋና ይኖሩ የነበሩ በሽዎች የሚቆጠሩ የአንጎላ ጥገኛ ዝሆኖችን ቦትስዋና ወደ ቀድሞ ከቀያቸው ወደሆነችው አንጎላ ለመመስ መወሰኗን ገልፃለች ተብሏል።

በጅብሪል ሙሀመድ
ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *