38 የህወሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት እስካሁን በተወሰደው የህግ የበላይነት የማስከበር ስራ 38 የህወሃት አመራሮች በህግ ጥላ ስር ውለዋል።

ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከልም የሰሜን እዝ የመረጃ ሰንሰለትን በመቁረጥ እና ሌሎች ወንጀሎችን ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ የመከላከያ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የህወሃት አመራሮት ይገኙበታል ተብሏል።

ይሁንና የእስር ትዕዛዝ ከወጣባቸው እና በፌደራል ፖሊስ ከተያዙ ተጠርጣሪዎች መካከል ከላይ ከተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ የተያዙትን ስም ዝርዝር ምክትል ኮሚሽነሩ አልተናገሩም።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ 298 የህወሀት አመራሮች ላይ ምርመራ ለማድረግና በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበራ ለማድረግ ትዕዛዝ ተላልፏል።

ምክትል ኮሚሽነሩ በጉዳዩ ዙሪያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ በመስጠት ላይ ሲሆኑ ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናደርሳችኋለን።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *