ሱዳን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የምታደርገው የአባይ ግድብ ሙሌት አስገዳጅ ስምምነት ሳይፈጸም መሆን የለበትም አለች።

ኢትዮጲያ ሕጋዊ እና አስገዳጅ ስምምነት እስክትገባ ድረስ የአባይን ግድብ ለሁለተኛ ጊዜ ለመሙላት እንደማትችል እና እንደማትቀበል ሱዳን ገልጻለች፡፡

የሱዳን የመስኖ እና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ያሲር አባስ ዘ ናሽናል ለተሰኘው የዜና አውታር እንደተናገሩት ለሁለተኛ ጊዜ ያለ ስምምነት መሞላት በሱዳን ደህንነት ላይ ስጋት ይፈጥራል ፡፡

ቅዳሜ ምሽት በሱዳን የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ የሱዳን የመስኖ እና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ያሲር አባስ እና ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦማር ካማሬልደን ይህ ቢሆንም ለመፍትሔው ግን ፈጽሞ ወታደራዊ እርምጃ እንደማይወስዱ ተናግረዋል።

በብሉ ናይል ላይ በራሷ ኃይል-ማመንጫ ግድቦች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ወይም ጉዳት እንዳያደርስ ኢትዮጵያ የተጠናቀቀውን የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ለማካሄድ ኢትዮጵያ በትብብር ትስማማ ዘንድ ሱዳን ትፈልጋለች ፡፡

በሶስቱም መንግስታት መካከል ለአስር ዓመታት የተካሄደው ድርድር በግድቡ ሥራ ላይ የወደፊት አለመግባባቶችን ለመፍታት ወይም የማያቋርጥ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችል ዘዴ እስካሁን አልተገኘም ፡፡

ሱዳን የአፍሪቃ የውሃ እና ወንዝ ባለሙያዎች ድርድሩ ላይ የበለጠ ንቁ ሚና እንዲሰጣቸው ያቀረበችውን ሀሳብ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ውድቅ ካደረጉ በኋላ ሱዳን ባለፈው ወር ከድርድሩ ራሷን አግልላለች ፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት በሐምሌ እና ነሐሴ ወራት 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ለማጠራቀም አቅዳለች ፡፡

እንደሚታወቀው የኢትዮጲያ የመጀመሪያ ሙሌት በስኬት ማጠናቀቋን ማሳወቋ የሚታወቅ ነው ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *