በቬንዝዌላ አወዛጋቢ ምርጫ የፕሬዝዳንት ማዱሮ አጋሮች የምክር ቤቱን አብላጫ ድምፅ አሸነፉ።

በግጭት በታጀበው ምርጫ የቬንዝዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አጋሮች የምክር ቤቱን አብላጫ ድምፅ አግኝተዋል፡፡
አነስተኛ የተቃዋሚዎች ተሳትፎ ነበረው በተባለው በዚህ ምርጫ ፤ በዚህ ምርጫ መሳተፍ አንባገነንነትን ለማጠናከር በተሰናዳ ድራማ ላይ እንደመሳተፍ ይቆጠራል ሲሉ ተደምጠዋል፤ ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፡፡

የምርጫው ምክር ቤት እንደገለፀው ከ 5.2 ሚሊዮን ድምፅ የማዱሮ አጋር የሆኑ ፓርቲዎች 67.6 በመቶውን አብላጫ ድምፅ አግኝተዋል፡፡
እንደ ምክር ቤቱ በምረጫ ማዕከላት ጥቂት ሰልፎች የተስተዋሉ ሲሆን መምረጥ ከሚችለው ዜጋ 31 በመቶው ብቻ ነው የመረጠው፡፡

የሆነው ሆኖ የምክር ቤቱ የበላይነት በማዱሮ ቁጥጥር ስር መሆን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የደቀቀ ኢኮኖሚ፣ የአሜሪካ ትልልቅ ማዕቀቦችና ፣ የዜጎች ስደት ፤የአሁኗ የቬንዝዌላ መገለጫዎች ናቸው፡፡

ያለጥርጥር ታላቅ ድል ሲሉ ማዱሮ ደስታቸውን በቴሌቪዥን ቀርበው የገለፁ ሲሆን ቬንዙዌላ አሁን አዲስ ብሔራዊ ምክር ቤት አላት ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::
ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም
በሔኖክ አስራት

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *