አሜሪካ ለሞሮኮ እጅግ ዘመናዊ 4 የጦር ድሮኖችን ለመሸጥ ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸው ተገለጸ፡፡

ተሰናባቹ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አራት እጅግ ዘማናዊና የተራቀቁ ሰው አልባ የውጊያ ድሮኖችን፤ ለአፍሪካዊቷ ሀገር ሞረኮ ለመሸጥ በዋሺንግተን ዲሲ እየተማከሩ መሆኑን ከደቂቃዎች በፊት ሮይተርስ መረጃውን ይዞ ወቷል፡፡

ድሮኖቹ አሜሪካ ስራሽ ሲሆኑ MQ-9ቢ የሚል ስያሜ ያላቸው እንደሆነ አማላክቷል፡፡

ስምምነቱ ከወራት በፊተ እንደተጀመራ የገለጸው መረጃው፤ ሞሮኮ ትላንት ሀሙስ ከስራኤል ጋር ግንኙነቷን መደበኛ ለማድረግ መስማማቷን ተከትሎ መሁኑን ነው ለመስማማት ጫፍ መድረሳቸውን የጠቆመው፡፡

ይህም የሞሮኮና የእስራኤል መደበኛ ግንኙነትን ለመተግበር መስማማታቸው ለአሁኑ ስምምነት መፈጸም ትልቅ ድርሻ እንደሚኖርው ነው ያስታወቀው፡፡

መሮኮ ድሮኖቹን ደህንቷን ለማሰጠበቅ በተለይ የባህር ቀጠናዋን እንደፈለገች ተንቀሳቅሳ ለመቆጣጠር እንደምተጠቀምባቸው የገለጸች ቢሆንመ፤ በምን ያክል ዋጋ እንደገዛቻቸው ግን መረጃው ያለው ነገር የለም፡፡

ሞሮኮ ምንም እንኳን ከእስራኤል ጋር ለሰላማዊ ግንኙነት ውል ብትፈጽምም ቅሉ፤ ድሮኖቹን በእጇ የምታስገባ ከሆን ግን፤ ወደፊት ከስራኤልና ከተቀናቃኟ አልጀሪያ ጋር እንዲሁም፤ በአካካቢው ደህነት ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደሚሆን ፖለቲከኞች እየገለጹ ይገኛሉ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8
ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *