የገቢዎች ሚኒስቴር በአምስት ወራት ውስጥ ከ126 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በአምስት ወራት ውስጥ ከ126 ነጥብ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ እና ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ተናግሯል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ በተደረገ ርብርብ በያዝነው በጀት ዓመት ከሐምሌ እስከ ህዳር ባሉት አምስት ወራት ብቻ 126 ቢሊዮን 835 ሚሊዮን 480 ሺህ 740 ነጥብ 99 ብር በመሰብሰብ 101 በመቶ አፈፃጸም ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ17.4 ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ አሳይቷል ብላል ወ/ሮ ኡሚ፡፡
የገቢ ዓይነቶች ድርሻ ሲታይ ከአገር ውስጥ ገቢ 80.96 ቢሊዮን ብር፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 45.77 ቢሊዮን ብር እና ከሎተሪ ሽያጭ 109.45 ሚሊዮን ብር ነው ገቢ ተገኝቷል ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡
በኮቪድ ወረርሽኝ ተፅዕኖ እና ወቅታዊው የፀጥታ ችግር ውስጥ ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገብ በርካቶች ይሳካል ብለው የማይገምቱት መሆኑኑም ወ/ሮ ኡሚ ተናግረዋል፡፡

የግብር ከፋዮቻችን በፈቃደኝነት ግብር የመክፈል፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት እና የዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች የእርፍት ቀናት ጭምር ስራቸውን በትጋት በመስራታቸው ውጤታማ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡

በታህሳስ ወር 21.33 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል በመሆኑ ይህን ዕቅድ ለማሳካት ግብር ከፍዮች እየተወጣችሁ ያላችሁትን ኃላፊነት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::
ዳንኤል መላኩ
ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *