ሰረገላ ሜትር ታክሲ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

በሴቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጠው ሰረገላ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል።

ሴቶች የመኪና አደጋን የማድረስ አጋጣሚያቸው አነስተኛ በመሆኑ እና ሴቶች አቅም ስላላቸውም ነው ሴት አሽከርካሪዎችን የመረጥነው ሲሉ የሰረገላ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቤተልሄም ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

ሰረገላ ደንበኞቹን አክብሮ በጥንቃቄ ና በጥራት የሚሰራ እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡የሰረገላ መስራች አቶ ኤልያስ ነጋሽ በበኩላቸው ሰረገላ ከአሽከርካሪዎቹ በተጨማሪ የማኔጅመንት አባላት አብዛኛዎቹ ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡

የትራንስፖርት ዘርፉ ሴቶችን ያገለለ መሆኑ ከጥንቃቄ አንጻር ብዙ ጉድለቶች ነበሩበት ያሉት አቶ ኤልያስ ሰረገላም ይሄን ችግር ለመቅረፍ ሀ ብሎ ጀምሯል ሲሉ አክለዋል፡፡

የምንጠቀማቸው መኪኖችም ከቴክኖሎጂና ከደህንነት አንጻር በሚገባ ተዘጋጅተንበታል ብሏል ሰረገላ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በመቅደላዊት ደረጀ
ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *