ወቅቱ ፈታኝ የሆኑ ወረሽኞች የተከሰቱበት በመሆኑ መደበኛ የሀክምና አገልግሉቱችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ ከመስጠት ረገድ የግል የጤና ተቋማት የድርሻቸውን እንዲወጡ የጤና ሚኒስትር አሳሰበ፡፡

የግል ሆስፒታሉች ማህረሰባዊ ሀላፊነታቸውን ከመወጣት አንጻር ጎድለት እንዳለባቸው ዶ/ር ሊያ ታደስ ተናግረዋል፡፡

ሁሉንም ነገር ለመንግስት መስጠት ተገቢ እንዳልደለ ዶ/ር ሊያ ተናግረው ፡፡በተለይ የቲቢ ፤የእናቶችና ህጻናት የህክምና የክትባት አገልገሎት የኤች አይ ቪ ህክምናና ክትትል ጨምሮ ሌሉች አንገብጋቢና አጣዳፊ የጤና ግልጋሉቱችን እኚህ ተቋማት በመስጠት ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

በሀገሪቱ ያሉት እኚህ የግል ጤና መስጫ ተቋማትም ለህብረተሰቡ ጥራት ያለውና ተመጣጣኝ ክፍያ የሚጠይቅ ግልጋሉሎት በመስጠት ዘርፉን ሊያግዙ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ዶ/ር ሊያ ይህንን ያሉት ትላንት በአዲሱ የሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የአላትዮን ጠቅላላ ሆስፒታል ባለ 64 ስላይስ ሲ.ቲ ስካን መሳሪያ ከኢትዮ ሊዝ ጋር በመቀናጀት ስራን ማስጀመሩን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ ፕሮግራም ነው፡፡

64 ስላይስ ሲ.ቲ ስካን መሳሪያ በአዲስ አበባ ባሉ ጥቂት የጤና ተቋማት ብቻ እንደሚገኝ መሆኑ በስነስርአቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ይህ ማሽን በክልሉ መዲና ሀዋሳ መምጣቱ ለአጎራባች ክልሉች ለደቡብ ክልል፤ለኦሮሚያ ጨምሮ ለሌሉችም የአገልግሉት ፈላጊዎች ትልቅ እረፍ የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯ፡፡

የሲዳማ ክልል 219 የግል የህክምና አገልግሉት የሚሰጡ ተቋማት ይገኛሉ፡፡

የአላትዮን ጠቅላላ ሆስፒታል ባለቤትና ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው ገ/መስቀል መንግስት የግል ዘርፉን እንዲያግዝ ጠይቀዋል፡፡

ያይኔ አበባ ሻምበል
ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.