የዓለማችን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀት መጠንና- ፋብሪካዎች

በፈረንጆቹ 2021 የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀት በአለማችን ከፍተኛ ማሻቀብ ሊኖር እንደሚችል የዩናይትድ ኪንግድም የአየር ንብረት ትንበያ መስሪያ ቤት ይፋ አድርጓል፡፡

ከዚህ የካረቦን ልቀት ዉስጥ ከሃምሳ በመቶ በላይ የሚሆነዉን የሚሸፍነዉ ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣው የልቀት መጠን መሆኑንም ጥናቱ አመልክቷል፡፡

መስርያ ቤቱ አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት ለከፍተኛ ስጋት የሚዳርግ መሆኑንና እንደ አዲስ ወረርሽኝ እንዳይሆን ስጋት ፈጥሮብኛል ሲል አንስቷል ፡፡

ለዚህም መንደርደሪያ አድርጎ ያመላከተው በአለማችን በ2020 ተከስቶ በነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት በአለማችን ላይ ያለው የኢኮኖሚ መዳከም እና እንደ ከዚህ ቀደሙ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅም መስራት ባለመቻላቸው ሳቢያ ይነሳ የነበረው የጎንዮሽ ጉዳታቸው በዛው ልክ አሽቆልቁሎ ነበር ብሏል፡፡

አሁን ግን የአየር ንብረት ትንበያ መስሪያ ቤት እንደገለጸው በዚህ ዓመት ጥንቃቄ ከጎደለው ከዚህ በፊት ከነበረው ልቀቱ 50 በመቶ በመሆን ከፍ ወዳለ ደረጃ ሊጨምር እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

አስከፊ እና ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን የሚችልን የአየር ንብረት ለውጥ ለማስቀረት የ 2015 የፓሪስን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በ 2021 እንደ ወሳኝ ዓመት መታየቱን የተናገሩት የአየር ንብረት ትንበያ መስሪያ ቤት በዘርፉ ሳይንቲስት የሆኑት ሪቻርድ ቤትስ ፤ከድንጋይ ከሰል ፣ ከዘይት እና ከተፈጥሮ ጋዝ የሚነድ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ፈጣን እርምጃ መውሰድ ጊዜው አሁን መሆኑን የሚጠቁም ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ተመራማሪዉ “በከባቢ አየር ውስጥ በሰው ልጅ የተፈጠረው የ ካርቦን ክምችት በከፍተኛ ደረጃ እየተፋጠነ ነው” ብለዋል ፡፡

እንደውም እርሳቸው የችግሩን ክብደት በማስረጃነት ለማሳየት እንደሞከሩት በአለማችን የካርቦን ልቀት ደረጃ እስከ 25 በመቶ ለማደግ ከ200 ዓመታት በላይ ፈጅቶ ነበር ያሉት ምሁሩ ፣ አሁን ግን ከ 30 ዓመታት በኋላ ብቻ ወደ 50 በመቶ ጭማሪ ላይ ደርሰናል ብለዋል ፡፡

ከነዳጆች የሚወጣው ልቀትና የደን ጭፍጨፋ በ 2021 ውስጥ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ በከባቢ አየር ውስጥ መከማቸቱን እንዲቀጥል ያደርገዋል ያሉት ሪቻርድ፣ ይህም መጠን ለመጀመሪያ ጊዜ ቅድሚያ ከነበረው በአስፈሪ ሁኔታ ከፍ ብሎ እንዲገኝ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

የካርበን ደረጃዎች በአየር ንብረት ሳይንቲስቶች ደህና ናቸው የሚባሉበትን ደረጃ ከረጅም ጊዜ በፊት ማለፉን አሳይቶናል ጥናቱ ያሉት ሪቻርድ፣ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2019 ማድሪድ ውስጥ በተካሄደው የአየር ንብረት ስብሰባ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በወቅቱ የጉዳዩ አሳሳቢነት ጠቃሚ ነጥብ” ተደርጎ ተቆጥሮ ነበር ብለዋል ፡፡

ባለፈው አመት የዓለማችን ኢኮኖሚ በኮሮና ቫይረስ የተመታ በመሆኑ በ2020 በከፍተኛ ሁኔታ ከወደቀ በኋላ ዳግም ተመልሶ በአሁኑ ወቅት እየበረከቱ ያሉት የበካይ ጋዝ ልቀቶች በአብዛኛው ወደ ቅድመ-ወረርሽኝ ደረጃ እንዲመለሱ እና ስጋት ውስጥ እንዲያስገባ አድርጎታል ሲል የአየር ንብረት ጥበቃ ጽህፈት ቤት ይገልጻል፡፡

ሆኖም ግን የአየር ንብረት አያያዛችን አንዳንድ ልቀቶችን ረገብ ሊያደርግ የሚችል እና የደን እድገትና ብዛት ላይ ትኩረት ከተደረገ ፣ በ 2021 ውስጥ የ ካርቦን ክምችት ከ2020 በፊት ከነበረው ውጥረት ሊቀንስ የሚችልበት እድል እንዳለዉም አስገንዝበዋል፡፡
ምንጭ፡- አልጀዚራ

በረድኤት ገበየሁ
ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *