መራጩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ሲ አይ ኤን ዊሊያም በርንስ እንዲመራ በእጩነት አቀረቡ።

የአሜሪካን የስለላ ተቋም ሲ አይ ኤ ን፤ በሙያቸው ዲፕሎማት የሆኑት ዊሊያም በርንስ እንደሚመሩት ጆ ባይደን መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ዊሊያም በርንስ በፕሬዝዳንት ኦባማ ዘመን ምክትል የውጪ ጊዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከ33 አመት በላይ የስራ ልምድ አላቸው፡፡

ዊሊያም በርንስ የሩሲያና የጆርዳንም አምባሳደር በመሆንም አገልግለዋል፡፡

በአሁን ሰአት ለአለም አቀፍ ሰላምና ሌሎች አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የማማከር ስራ የሚሰራው Carnegie Endowment for International Peace ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ ነው፡፡

የዊሊያም በርንስ የሲ አይ ኤ አለቅነት የሚፀድቀው በአሜሪካ ሴኔት አብላጫ ድምፅ ሲያገኝ ሲሆን ከተሳካላቸው በሲ አይ ኤ የመጀመርያዋ ሀላፊ ሆነው እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 የተሾሙትን ጂና ሀስፔልን የሚተኩ ይሆናል፡፡

በሔኖክ አስራት
ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *