ብልጽግና ፓርቲ በአገር አቀፍ ደረጃ 10 ሚሊዮን ገደማ አባላት እንዳሉት አስታወቀ።

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን የ2013 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማውን በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል።

ይህ ኮሚሽን በዋናነት የፓርቲው መርሆዎች፣ እሴቶችና አሰራሮች በጥብቅ ዲሲፕሊን መመራታቸውን መከታተል ነው።

ኮሚሽኑ በዚህ የግምገማ መድረኩ ላይ እንዳለው በአገር አቀፍ ደረጃ 9 ሚሊዮን 941 ሺህ 467 አባላት እና አመራሮች እንዳሉት ገልጿል።

በመድረኩ ኮሚሽኑ የ6 ወር ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮችም የራሳቸውን ሪፖርት አቅርበው ውይይት መካሄዱን ብልጽግና ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም
የኢትዮጵያዊያን
ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *