በአዲስ አበባ እና ዙሪያ በጥምቀት በዓል ዕለት በደረሱ ሁለት የእሳት አደጋዎች ምክንያት ከ250 ሺህ በላይ ብር ንብረት መውደሙ ተገለጸ።

የመጀመርያው አደጋ የደረሰው በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ በአንድ መኖርያ ቤት ላይ በኤሌክትሪክ ንክኪ የተከሰተ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በአደጋው ምክንያትም ከ10ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማትረፍ የተቻለ ሲሆን አንድ መቶሺህ ብር የሚገመት ንብረት ደግሞ መውደሙን ነው የተገለጸው፡፡

የእሳት አደጋው ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ዘጠኝ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ሁለት የአደጋ መከላከል ተሸከርካሪዎች መሰማራታቸው ተነግሯል፡፡

እንደዚሁም እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል 6ሺህ ሊትር ውሀ ለአገልግሎት ውሏልም ተብሏል፡፡

ሌላው አደጋ የደረሰው ደግሞ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ወለቴ አካባቢ በሚገኝው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 26 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና አምስት ተሸከርካሪዎች መሰማራታቸውን ተነግሮ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው ተብሏል፡፡

በአደጋው 150 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን አደጋውን ቶሎ መቆጣጠር በመቻሉ ምክንያት ከ700 ሺህ በላይ ብር ማዳን መቻሉን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግ ንኙነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *