የፅንፈኛው ህወሓት ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጡ::

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትና በጡረታ በክብር የተሰናበቱት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን የአገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እጃቸውን የሰጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የፅንፈኛው ህወሓትን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት ላይ የነበሩ ናቸው።

መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ጁንታውን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ የፅንፈኛው ህወሓት ጥቃት በፈጸመበት ወቅትም ዋና አስተባባሪ የነበሩ ናቸው።

ምንጭ፡ ኢዜአ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *