የፈረንጆቹ አዲሱ አመት 2021 ከገባ ወዲህ 43 አፍሪካውያን ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር መሞታቸው ተገለጸ።

አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አዲሱ አመት ከገባ በ21 ቀናት ውስጥ ብቻ፤ በሊቢያ አድርገው ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመግባታ በሚሞክሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ውስጥ፤ 43 የሚሆኑት የሚሄዱበት ጀልባ ተገልብጦ መሞታቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

ያሳለፍነው ማክሰኞም ቢሆን ከሊቢያ ወደብ ከተማ ዛውያ ተነስቶ ስደተኞችን ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ ጀልባ በሜዲትራንያን በህር ላይ ትንሽ ርቀቶችን እንደተጓዘ መገልበጡንም ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ስደተኞቹ ከኮትዲቯር፤ ከናይጀርያ፤ ከጋና፤ ከጋምቢያና በአብዛኛው ከምእራብ አፍሪካ ሃገራት የመጡ መሆናቸውን የጠቆመው ድርጅቱ፤ የሟቾች ቁጥርም ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችልም ነው ያመላከተው፡፡

ከአደጋው ለተረፉት ስደተኞችም ተገቢውን የሰብአዊነት እርዳታ አለም አቀፍ ከሆኑ ረጂ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጥሪ አቅርቧል፡፡፡

በጅብሪል ሙሀመድ
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *