የሀገር ውስጥ ዜና

የጎንደር ዩንቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸዉን ከ6 ሺ በላይ ተማሪዎችን በነገዉ እለት ያስመርቃል።

ዩንቨርሲቲዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ድግሪ በሁለተኛ፤ በሶስተኛና በሰብ ሰፔሻል የህክምና ትምህርት 6 ሺህ 688 ተማሪዎች በነገዉ እለት ይመረቃሉ ብሏል፡፡

የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተማሪዎቹ ኮቪድ 19 ተፅእኖ ተቋቁመዉ ለፍሬ የበቁ በመሆናቸዉ ምረቃዉን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

የጎንደር ዩንቨርሲቲ ባለፈዉ አመት በበይነመረብ አማካኝነት ተማሪዎችን እንዳስመረቀ ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ በነገዉ እለትም የ6ሺህ 688 ተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርአት ወላጆቻቸዉ በተገኙበት በዩንቨርሲቲዉ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

የዚህ ዓመት ተመራቂዎች በርካታ የሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ችግሮችን እና ውጣ ውረዶችን አልፈው ለዚህ የበቁ በመሆናቸው ከሌሎች ጊዚያት ተመራቂዎች ልዩ ያደርጋቸዋል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

የምረቃ ስነ ስርዐቱ ሲከናወንም ኮቪድ 19ን በመከላከል ሊሆን እንደሚገባ ያሳሰቡት ዶክተር አስራት ፤ተመራቂ ተማሪዎቻችን የተመራቂ ቤተሰቦች፣ እና እንግዶችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን ካልያዙ ወደ ግቢ እንደማይገቡም ዩንቨርስቲው አሳስቧል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዐቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸዉ የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጎንደር ዩንቨርሲቲ ኮቪድ 19ኝ ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ከዩንቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ሰምተናል፡፡

በአባቱ መረቀ
ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *