የስምንት ዓመቱ ታዳጊ ከናይኪ ጋር ተፈራረመ::

ሜሲ ከናይኪ ጋር የመጀመሪያ ኮንትራቱን የተፈራረመው በ15 ዓመቱ ነበር፡፡ ኔይማር ደግሞ በ13 ዓመቱ፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን ከሚከሰቱ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ የስምንት ዓመቱ ካዋን ባሲል ከናይኪ ጋር የመፈራረም ዕድል ያገኘው በዚህ ምክንያት ነው፡፡

በቀላሉ ተሰጥኦን ማሳየት የሚቻልበት ጊዜ ላይ በማደጉ ከኔይማር እና ሊዮኔል ሜሲ ባነሰ ዕድሜ ዕድሉን ያገኘው ለዚያ ነው፡፡

ገና በለጋ ዕድሜው የብራዚል እግር ኳስ የመጪው ዘመን ተስፋ ተደርጎ መታየት ጀምሯል፡፡ አሁን ባለበት ዕድሜ እና ብቃቱን አውጥቶ ማሳየት በሚጠበቅበት 18 ዓመት ዕድሜው መካከል ግን ብዙ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮች አሉ፡፡

ባሲል ከትጥቅ አምራቹ ኩባንያ ናይኪ ጋር ያደረገው ስምምነት ለሶስት ዓመት የሚዘልቅ ነው፡፡ ታዳጊው በትክክለኛው ጎዳና የሚጓዝ ከሆነ ስምምነቱ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ሊቀጥል እደሚችልም ተጠቅሷል፡፡

አባቱ አንድሬዚንሆ የኮረንቲያንስ የቀድሞ ተጫዋች ነበር፡፡ ልጁ የተጠበቀውን ያህል መሆን የሚችልበት ዕድል እዳለውም ይናገራል፡፡ ‹‹ከፍተኛ የማሸነፍ ፍላጎት ያለው ተጫዋች ነው፡፡ በርካታ ድንቅ የቴክኒክ ክህሎቶችን ታድሏል›› በማለት አንድሬዚንሆ ያብራራል፡፡

በአቤል ጀቤሳ
ጥር 19 ቀን 2013

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *