በኢትዮጵያ ካሉ 70 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሴት ከፍተኛ አመራሮች ያሏቸው ፓርቲዎች ሁለት ብቻ እንደሆኑ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስርዓተ-ፆታ አካታችነት ኦዲትን ሀገራዊ ጥናቱን ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።

በዚህ ጥናት መሰረት አንድ ሴት መሪ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ተፎካካሪ ፓርቲ ሲሆን መሪዋም ወ/ሮ ቆንጂት ብርሃን መሆናቸው ተገልጿል።

ሁለተኛዋ ምክትል መሪ ደግሞ ከአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ተፎካካሪ ፓርቲ ሲሆን ወ/ሮ ማርታ ካሳ መሆናቸው ታውቋል።

የጥናት ውጤቱን ያቀረቡት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስርዓተ ፆታና ማህበራዊ ጉዳዮች ሃላፊ ወ/ሮ መድሃኒት ለገሰ እንዳሉት፣ በጥናቱ በአባልነት ለመመልመል በፓርቲ መዋቅሮች ውስጥ የውሳኔ ሰጭነት ቦታዎችን በመያዝ ረገድ ሊደረግ የሚችል በፆታ ላይ የተመሰረተ አድልዎን በግልፅ የከለከሉ ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ከሰባዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ደግሞ በ21 ፖለቲካ ፓርቲዎች በፓርቲ መዋቅር ኮሚቴዊች ውስጥ ማለትም በማእከላዊ ኮሚቴ፣ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ኦዲት ኮሚቴ ውስጥ ተካተዋል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ሴቶች በፓርቲ መዋቅር ውስጥ እንደ ኮሚቴ መሪ ወይም እንደ ምክትል ሃላፊ ሲሆኑ ግን አይታዩም ብለዋል።

በጥናቱ ከተካተቱት ውስጥ ደግሞ 21 በመቶ ወይም 15 የሚሆኑት ፓርቲዎች ብቻ በፖለቲካ ፓርቲያቸው የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ የስርዓተ-ፆታ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ለመፍታት የሚያስችል መዋቅር አለቸው።

ከነዚህ ውጪ ያሉ ብዙዎቹ ፓርቲዎች ደግሞ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት አንድ አይነት የስርአተ ፆታ እኩልነት ወይም የሴቶች መብቶች ጉዳዮችን በፓርቲያቸው ሰነዶች ውስጥ አካተዋል ብለዋል።

ወ/ሮ መድሃኒት ለሴቶች ምቹ ያልሆኑ የውስጠ ፓርቲ መዋቅሮች መኖራቸው፣ የሴቶች ጥቃትን መሰረት ያደረጉ የፖለቲካ ባህል መኖሩ፣ በስርዓተ ፆታ ተፅእኖ ስር የወደቀ የስርእተ ፆታ ግንኙነት መኖሩ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ እንዲሆኑ ያደረጉ ምክንያቶች መሆናቸውን በጥናቱ ጠቁመዋል።

በመሆኑም በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሴቶች በአባልነት በመሪነትና በፖለቲካው ምህዳር ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን ላይ ሃሳብ ማንሸራሸር፣ ሴቶች በፖለቲካ መድርኮች እንዲሳታፉ ማመቻቸት፣የስርዓተ ፆታ መዋቅሮችንና አጀንዳዎችን ማውጣትና በትክክል መተግበር፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያለውን የተሳሰሰተ አመለካት ማስተካከል፣ የህግና የፖሊሲ ማእቀፎች በተለይም የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ በፖለቲካው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በጅብሪል ሙሀመድ
ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *