ኢትዮጵያ የቀጣይ አስር አመት የትራንስፖርት መሪ እቅዷን ለማሳካት ከ3 ትሪሊየን ብር በላይ ያስፈልጋታል ተባለ፡፡

የትራንስፖርት ዘረፍ የአስር አመት መሪ የልማት እቅዱን ለማሳካት 3 ነጥብ 04 ትሪሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡

ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 69 ነጥብ 55 ቢሊየን ብር በዘርፉ ከሚሰጠው አገልግሎቶች በሚሰበሰበው ገቢዎች የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል፡፡

የተቀረው ደግሞ ከመንግስት በጀት ከብድር እና ከውጪ ከሚገኝ እርዳታ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደተናገሩት የትራንስፖርት ዘርፍ የአስር አመት መሪ የልማት እቅድ

በማዘጋጀት ባለፉት የእቅድ ዘመናት ዘርፉ ያላሳካቸውን እቅዶች ምክንየታቸው በመለየት ለህብረተሰቡ ፈጣንና የተሟላ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡

እንደዚሁም የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ እቅድ ተግባራዊ መሆን በተለያዩ ጊዜያቶች ይነሱ የነበሩ የተጠቃሚነት እና ተደራሽነት ጥያቄዎችን የሚመለስ በመሆኑ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *