ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጤና ሚኒስቴር ሥር የሚገኘውን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጤና ሚኒስቴር ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘውን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡

የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅት በተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች አካላቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ በማምረት የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡

ከውጭ መጥተው በበጎ ፈቃደኝነት ይሄንን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ወገኖች ሊበረታቱ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጻዋል፡፡

ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *