በኢትዮጵያ የግንባታ ስራዎች ባልተገባ መንገድ በተወሰኑ ስራ ተቋራጮች እጅ እየገባ መሆኑን አስታወቀ።


የመንግስት ተቋማት በሚከተሉት ያልተገባ አሳር ምክንያትም ከ22 ሺህ በላይ ስራ ተቋራጮች ውስጥ አብዛኞቹ ስራ ተቋራጮች ስራ እያገኙ አለመሆኑን ማህበሩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር በተለያዩ መንግስታዊ ግዢ ፈፃሚ መ/ቤቶች በኩል የሚታዩ ኢ-ፍትሃዊ የግንባታ አግልግሎት ግዢ አፈፃፀሞች አሉ ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

የማህበሩ ፕሬዘዳንት ኢንጅነር ግርማ ሀ/ማርያም እንዳሉት በሀገራችን አብዛኛው የግንባታ አገልግሎት ግዢ የሚፈፀመው በመንግስታዊ ተቋማት ነው።
ተቋማቱ ደግሞ ግዥውን ሲፈፅሙ ከሚከተሏቸው መመሪዎች ባፈነገጠ መንገድ መሆኑን አመላክተዋል።
ይህ ደግሞ የግንባታ ስራዎች በተወሰኑ ስራ ተቋራጮች እጅ እንዲገባና አብዛዎቹ ስራ ተቋራጮችን ስራ እንዳያገኙ አደርጓል ብለዋል።

ኢንጅነር ግርማ በአሁኑ ሰአት በባንኮች የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ቦንድ ጋር ባሉ ችግሮች እንዲሁም ከባንክ ውጪ የሚደረገው በጥሬ ገንዘብ 75 ሺህ ብር ብቻ መሆኑ ሌላው ችግር ነው ብለዋል።

በዋና ዋና የግንባታ ግብአቶች ላይ ከፈተኛ የዋጋ መናር መኖሩን የጠቆሙት ኢንጅነር ግርማ፤ ዘርፉን እየፈተኑ ያሉ ችግሮችን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ እየተወሰኑ ያሉ የውል ማማቋረጥ ውሳኔዎች መከሰታቸውንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በግንባታ ስራ አሰጣጥ ሂደቶች ሰፊ ችግሮች መኖራቸውንም እንዲሁ ተናግረዋል።
በመሆኑም እንደ ሀገር እያደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ለማስቆም ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት የጋራ ትብብር ሊደረግልን ይገባል ብለዋል።
በጅብሪል ሙሀመድ
ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.