የሸማቾች ጥበቃ እና ውድድር ባለስልጣን ሸማቾችን ያሳስታሉ በሚል 3 ማስታወቂያዎችን አገደ።

ባለስልጣኑ ከአዋጁ ጋር የሚጻረሩ የንግድ እቃዎችና የአገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ገልጿል።

በግማሽ ዓመት አፈፃፀም የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለ ስልጣን ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከአዋጅ ቁጥር 813/2006 ጋር የማይጣጣሙ የንግድ ዕቃዎችና የአገልግሎት ማስታወቂያዎችን 48 ጊዜ በመከታተል እና ከአዋጁ ጋር የሚፃረሩ የንግድ ማስታወቂያዎች ላይም በግማሾቹ ላይ የማስታወቂያ እግድ ሲወጣ ቀሪዎቹ ላይ ይዘታቸው እየተጣራ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ሲተላለፉ የነበሩ ከሴራሚክ ሽያጭ፣ የቀለም ሽያጭ፣ ከዲኮደር ሽያጭ፣ ከታሸገ ዉሃ ማስታወቂያ እና ለትራንፖርት አገልግሎት ከሚዉሉ ታክሲዎች ከቀረጥ ነፃ አቅርቦት ጋር በተገናኘ የሚተላለፉ የንግድ ማስታወቂያዎች ግልፀኝነት የጎደላቸዉና ሸማቹን ሊያሳስቱ ይችላሉ በማለት 3ቱ ሲታገዱ የ 2 ማስታወቅያዎች ይዘት እየተጣራ ይገኛልም ተብሏል በሪፖርቱ፡፡

በተጨማሪም የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓላትን ምክንያት በማድረግ በ14 የሴትና የወንድ ልብስና ጫማ መሸጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ፈርኒቸር መሸጫ የንግድ መደብሮች ስለዋጋ ቅናሽ የተለጠፉ የውጭ ማስታወቂያዎች ላይ ክትትል በማድረግ በ 10 የንግድ መደብሮች የተለጠፉ የንግድ ማስታወቂያዎች ግልፀኝነት የጎደላቸው እና አሳሳች ናቸው ተብለዋል፡፡

በዚህም በአዋጁ አንቀፅ 7 እና 8 መሠረት ማስታወቂያዎችን እንዲያስተካክሉ ከመደረጉም በላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለወደፊቱ እንዳይፈፅሙ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡

በተያያዘም የህትመት ሚዲያ ላይ አሳሳች ማስታወቂያዎችን ከመከታተል አንፃርም የተለያዩ የህትመት ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ የሚገኙ የንግድ ማስታወቂያዎች ይዘት ትክክለኛ ስለመሆኑ ምርመራ እንዲጀመር ተደርጓልም ተብሏል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *