አሜሪካና ሩሲያ የኒኩለር ጦር መሳሪያ የሚቆጣጠረዉን ስምምነት ለማራዘም ተስማሙ።

ዋሺንግተን እና ሞስኮ የጦር መሳሪያ ትጥቅን የሚገድበዉ ስምምነት እስከ 2026 ድረስ ለማራዘም መስማማታቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

በነገዉ እለት ይጠናቀቅ የነበረዉ የእገዳ ስምምነቱፕሬዝዳንት ባይደን ለቀጣዮቹ 5 አመታት ድረስ ተግባራዊ እንዲሆን ከሩሲያዉ አቻቸዉ ቪላድሚረ ፑቲን ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የሁለቱ አገራት የኒኩለር ጦር መሳሪያ ገደብ ስምምነት አህጉር አቋራጭ ሚሳኤሎችንና ቦምቦችን መታጠቅን የሚከለክል እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን የቀድሞዉ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ቃል ኪዳን እንዲራዘም ፍላጎት አልነበራቸዉም ተብሏል፡

አሁን ላይ ግን የባይደን አስተዳደር እንዲራዘም መፍቀዱን ተከትሎ ስምምነቱ ለሁለቱም አገራት ድል ከመሆኑም በተጨማሪ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ነዉ ተብሎለታል፡፡

የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም ዉሳኔዉ ከሩሲያ መንግስት ጋር በቅርበት እንድንሰራ ያስችለናል ማለታቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

ፕሬዝዳንት ባደንም ይህ ስምምነት የ21ኛዉ ክፍለ ዘመንን የአለም የፀጥታ ችግር ለማጋገጥ የመጀመሪያዉ ምእራፍ ብለዉታል፡፡

በአባቱ መረቀ
ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *