በስምንት ክልሎች የሚገኙ 25 ከተሞችን መብራት እንዲያገኙ የሚያስችል የ20 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈረመ።

ይህ ስምምነት የገጠር ከተሞችን በፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግን መሰረት ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ ፕሮጀክት በስምንት ክልሎች በተመረጡ ከተሞች እና ቀበሌዎች የሚገነባ ሲሆን፤ በአራት ስራ ተቋራጮች በ6 ሎት ተከፈሎ ይገነባል ተብሏል።

በሎት አንድ በአማራ ክልል፦ ታች አርማጭሆ ወረዳ ደለሳ ከተማ/ቀበሌ፣ምስራቅ በለሳ ወረዳ አርባ ፀጉር ከተማ፣ ተኩሳ ወረዳ በግ መንክር ከተማ፣ አለፍ ወረዳ ፈንጅት ከተማን እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፦ ጉባ ወረዳ አልማሃል ከተማ በዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

በሎት ሁለት ዳራቶሌ ወረዳ ዳራቶሌ ከተማ፣ ሂግሎለይ ወረዳ ሂግሎለይ ከተማ ፣ በኦሮሚያ ክልል አሬሮ ወረዳ መልካሃሉ ከተማ ሲሆን
በሎት ሶስት በሶማሌ ክልል፦ በኮሎማዩ ወረዳ በኮሎማዩ ከተማ፤

በሎት አራት በኦሮሚያ ክልል፦ አና ሶራ ወረዳ አደሌ ከተማ፣ ጎሎልቻ ወረዳ ድሬ ሸክ ሁሴን ቀበሌ፣ ሃዊ ጉዲና ወረዳ ቢሊቃ ከተማ፣ ሃዊጉዲና ወረዳ ቃበናዋ ከተማ፣ አና ሶራ ወረዳ ሳይ ከተማ፣ ጉራዳሞሌ ወረዳ ሆኮልቱ ከተማ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

ሎት አምስት ፦ በደቡብ ክልል፦ ሱርማ ወረዳ ኪቢሽ ከተማ፣ ቱም ወረዳ ማጂ ከተማ፣ ሰላማጎ ወረዳ ሃና ከተማ፣ ዳሰነች ወረዳ ደለግኑመር ከተማ፣ በኦሮሚያ ክልል ዲሎ ወረዳ ሲጊርሶ ከተማ

እንዲሁም በሎት ስድስት ፦ በአማራ ክልል፦ ጠገዴ ወረዳ እርጎዬ ከተማ
በትግራይ ክልል ደግሞ፦ እንደመሆኒ ወረዳ ውህደት ከተማ፣ ፀለምቲ ወረዳ ፍየል ውሃ ከተማ በጋምቤላ ክልል፦ ዋንቶዋ ወረዳ ሜጣር ከተማ በአፋር ክልል ዳሎል ወረዳ ባዳ ከተማ ናቸው።

በዚህ ፕሮጀክት ግንባታ ሶስት የቻይናና አንድ የኮርያ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን በ6 ወራትም ይጠናቀቃል ተብሏል።

የዚህ ፕሮጀክት የገንዘብ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክና መንግስት (የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት) ሲሆኑ አጠቃላይ ወጪው 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 161 ሚሊዮን የኢትዮጲያ ብር ነው።

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *