በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሶስት ሰው ህይወት አለፈ፡፡

በአዲስ ትናንት እና ከትናንስ በስቲያ በተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል።

የመጀመርያው የሞት አደጋ የተከሰተው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት የ29 አመት ሴት ልጅ ወንዝ ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል፡፡

ሌላው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሁለት ወጣት ወንዶች ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሂወታቸው ማለፉን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና በከተማዋ በደረሱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች በሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ መድረሱን ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል፡፡

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት በመኖርያ ቤት እና በሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ ሁለት ወጣቶች በአደጋው ከባድ ቁስለት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

በዚሁ አደጋ ምክንያትም ሁለት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን 12 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *