በእንግሊዝ አሁንም ሌላ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ተገኘ።

በእንግሊዝ የኢንዲንበርግ ዩኒቨርስቲ ተማራማሪ ሳይንቲስቶች ከቆየውና በቅርብ ጊዜ ከተከሰቱት የዩኬና የደቡብ አፍሪካ ዝርያዎች የተለየ አዲስ የኮሮና ቫይረስ አይነት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

አዲሱ ኮሮና ቫይረስ ተመራማሪዎቹ B.1.525 የሚል ስያሜን የሰጡት ሲሆን ቫይረሱ በተገኘበት አካባቢ በተደረገ የቤት ለቤት ምርመራ ሊታወቅ እንደቻለ ነው ያስታወቁት።

የዚሁ አይነት ቫይረስም በእንግሊዝ ከታየ በኋላ በዴንማርክ፣ በአሜሪካና በናይጀሪያ ታይቷል ብለዋል ሳይንቲስቶቹ።

ይሄው አዲሱ ቫይረስ ከነበሩት ቫይረሶች የበለጠ ተላላፊ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በተለይ ደግሞ ወደ ሰውነት የሚገቡ እንግዳ ነገሮች ከሰውነት ጋር ተስማሚ በማይሆኑበት ጊዜ እንዲሁም በሰዎች ውስጥ በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅምን ሊያዳክም የሚችልበት አመላካች ነገሮች አሉት ይላሉ።

እንዲሁም አሁን የተዘጋጁትንና በጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉትን ክትባቶች መቋቋም የሚያስችለው ነገር ሊኖረው ይችል ይሆናል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

ቢሆንም ግን አዲሱ ቫይረስ ገና ጥናት የሚያስፈለገው ነው፣ በባህሪው ዙሪያ በምርምራ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደዚህ ነው ብሎ መናገሩ ስህተት ነው ፣ አዲስ የኮሮና ቫይረስ መሆኑን ግን በእርግጠኝነት መናገር እናፈልጋለን ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል መሀመድ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *