በትራንስፖርት ቢሮ የኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ዛሬ ተደረገ የተባለዉ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሬ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትን አያካትትም፡፡
በመሆኑም የሸገር፣ አንበሳና ድጋፍ ሰጭ አዉቶቡሶች ቀደም ሲል በነበራቸዉ ታሪፍ የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዉናል፡፡
ምክንያቱን ሲያስረዱም ለእነዚህ ድርጅቶች የከተማ አስተዳደሩ በየአመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ድጎማ ስለሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በየቀኑ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አቶ አረጋዊ ተናግረዋል፡፡
በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም
