የዘንድሮው የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ አባል ሀገራት ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል፡፡

በናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ አባል አገራት መካከል የሚደረገው አመታዊ ስብሰባ ዛሬ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በበይነ መረብ መካሄድ እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡

የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ከኡጋንዳ መንግስት ጋር በመተባበር በናይል ወንዝ ቀጠና የሚገኙ ሀገራትን በማስተባበር የናይል ቀንን ለማከበር ሲባል የተቋቋመ ነው፡፡

በስብሰባው የተፋሰሱ አባል ሀገራትን ጨምሮ፤የአካባቢ እንክብካቤ፤ የሀይል ልማት ፤የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት፤ ተመራማሪዎና የሲቪክ ማህበራት፤ ብዙሃን መገኛዎች ይታደማሉ ተብሏል፡፡

ኢኒሼቲቩ የተፋሰሱ ሀገራትን በማሰባሰብ በሀገራቱ መካከል የልምድ ልውውጥ ይደረግበታል ተብሏል፡፡

እንዲሁም የተፋሰሱ ሀገራት በናይል ወንዝ ዙሪያ እንዴት በጋራና በፍትሃዊነት ተጠቃሚ ሊሆኑባቸው በሚችሉባቸው ነጥቦች ዙሪያ ምክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ከ22 ዓመት በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ በዘጠኝ የአባይ ወንዝ ተፋሰስ አገራት በዩጋንዳ ኢንቴቤ የተመሰረተ ተቋም ነው።

ይህ ተቋም በዋናነት በአባይ ወይም በናይል ወንዝ ላይ ፍትሀዊ የውሃ ልማት እንዲመጣ፤በአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረቱን ያደርጋል።

በኢትዮጵያ፤ዩጋንዳ፤ኬንያ፤ሱዳን፤ግብጽ፤ታንዛንያ፤ቡሩንዲ፤ ሩዋንዳ የተመሰረተ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ኤርትራ በታዛቢነት ሲቀላቀሉ ደቡብ ሱዳን ከምስረታው በኋላ አዲስ አገር መሆኗን በህዝበ ውሳኔ ማወጇን ተከትሎ ተቋሙን ተቀላቅላለች።

በጅብሪል መሀመድ
የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *