በመተከል ዞን በሁሉም ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያዎች ተከፈቱ፡፡

የፀጥታ ችግር በነበረበት የቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ላይ በሁሉም ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ መክፈቱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

በመተከል ዞን በሚገኙት 7 ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ መከፈቱን ያስታወቁት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ናቸው፡፡

ምርጫ ቦርድ በዛሬው እለት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚሁ ውይይት ላይም በስድስት ክልልሎች ላይ የእጩ ምዝገባ መጀመሩን ዋና ሰብሳቢ አስታውቀዋል ተናግረዋል፡፡

የእጩ ምዝገባው የተጀመረባቸው ቦታዎችም
አዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲሆኑ
በተቀሩት ክልሎች ደግሞ ከዛሬው እለት ጀምሮ የእጩ ምዝገባ ሂደቱን ይጀምራሉ ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *