ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ባለው የድንበር ውዝግብ የትኛውንም ወገን አስታርቁኝ ብላ አለመጠየቋን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።

ሱዳን በህገወጥ መንገድ ከያዘችው መሬት የምትወጣ ከሆነ ኢትዮጵያ ለድርድር ዝግጁ መሆኗንም አስታውቃለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የያዘውን መሬት ለቆ በፊት ወደነበረበት ቦታ ከተመለሰ ኢትዮጵያ ትደራደራለች ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በመስጠት ላይ ሲሆኑ በዚህ ወቅት እንዳሉት ሱዳን የያዘችውን መሬት በለቀቀችበት ቅፅበት ኢትዮጵያ ወደ ውይይት ትመለሳለች ብለዋል።

በርካታ የጎረቤትና ሌሎች የአለም አገራት እናስታርቃችሁ የሚል ጥያቄ እና ፍላጎት እንዳላቸው የገለፁት አምባሳደር ዲና ይህ ግን ሊታይ የሚችለው ሱዳን ወደነበራት ይዞታ ስትመለስ ብቻ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ቱርክን ከሱዳን ጋር አሸማግሊኝ ብላ ጠይቃለች ተብሎ የሚወራ ከእውነት የራቀ ነውም ተብሏል።

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ የሁለቱ አገራት ጉዳይ በመሆኑ ችግሩን መፍታት የሚገባው በሶስተኛ ወገን ሳይሆን በባለጉዳዮቹ እንደሆነም ቃል አቀባዩ አንስተዋል።

በሌላ በኩል የህዳሴው ግድብ ውይይትን በተመለከተም ኢትዮጵያ ሌላ አደራዳሪ እንደማትፈልግም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል ።

በአባቱ መረቀ
የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *