የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት 26 ቢሊዮን ብር መክሰሩን ተገለፀ።

ድርጅቱ እንዳስታወቀው መንግስት ሰሞኑን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ በማድረጉ ምክንያት የ26 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ደርሶብኛል ብሏል።

እኛ መንግስት በሊትር ላይ ጭማሪ እንዲያደርግ ጠይቀን የነበረው 8 ብር ነበር ይሁንና ጭማሪው በሊትር 3 ብር ብቻ መሆኑ ድርጅቱን ለ26 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ዳርጎታል ብሏል።

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የነዳጅ እና ነዳጅ ውጤቶች ትስስር እና ስርጭት ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ቱሳ እንዳሉት በተደረገው ማሻሻያ መሰረት የ5 ብር ልዩነት ተፈጥሯል ይህን ልዩነት በቀጣይ ቀስ እያልን የዋጋ ማስተካከያ ይደረጋል ብለዋል።

ከፍተኛ የሆነ የሎጀስቲክ እጥረት ለነዳጅ እጥረቱ ምክንያት እየሆነ ነው ያሉት አቶ አህመድ የማደያ መጠኑም ዝቅተኛ መሆን ዋናው ምክንያት እንደሆነም ተናግረዋል።

አጠቃላይ በኢቲዮጵያ ያሉት ማደያዋች 1100 ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ከዛም በተጨማሪ ማደያዋች ሰው ከሚበዛበት ይልቅ ጫካ ላይ እና ዳር ዳር አካባቢ መገንባታቸውም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የነዳጅ ቦቴ ተሽከርካሪዎች ከ 2500 በላይ ቢመዘገቡም በስራ ላይ ያሉት ግን 2200 አካባቢ ነው ተብሏል።

የጥቁር ገበያ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት የራስ ምታት ሆኗል፤ ሰሞኑን የተወሰነ የዋጋ ልዩነቱ መደረጉን ተከትሎ ከደሴ አካባቢ ናፍጣ እና ቤንዚን እየቀላቀሉ እየሸጡ መሆኑንም ተጠቁመናል ብለዋል።

እርሱም ላይ ክትትል እናደርጋለን
በ 1 አመት ውስጥ በመመረያ እና በአሰራር ጥቁር ገበያን እናጠፋለን ብለዋል።

ድርጅቱ በቀጣይ ተጨማሪ 400 ቦቴ መኪና ግዢ እንደሚፈፀም አቶ አህመድ ተናግረዋል።

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.