የባንኩ ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ አከባበሩን አስመልክቶ በአዲስ አበባ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።
25ኛ አመት በአሉን አስመልክቶ በነገው ዕለት ባንኩ ስፖንሰር በማድረግ በ20 አውቶቡሶች ላይ የነጻ አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ለባንክ ኢንደስትሪ በማስተዋወቅ ፈር ቀዳጅ ነው ተብሏል።
ባንኩ ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ካርድና የባንክ መረጃን በአንድ ቋት መስራትን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
ከዳሽን ተራራ ስያሜውን የወሰደው ባንኩ 25ኛ አመቱን አስመልክቶ ወደ ዳሽን ተራራ የሚደረግ የከፍታ ጉዞ የተሰኘ ቋሚ የአብሮነት ጉዞ ሊያዘጋጅ ማሰቡንም አስታውቋል
በመቅደላዊት ደረጀ
የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም
