በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ታመመ በተባለ አንድ ሰራተኛ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት ዳግም ተጀመረ።

የተሽከርካሪ የፍጥነት መገደቢያን በተመለከተ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስርያ ቤት አገልግሎት የሚፈልጉ ባለ ጉዳዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንዳልቻሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታ አቅርበው ነበር፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንደሚሉትም ከሆነ ከተሽከርካሪ የፍጥነት መገደቢያ ጋር በተያያዘ ደብዳቤ ላይ የሚመታልን መሃተም ቢኖርም ከባለስልጣኑ መስርያ ቤት ግን ይህን አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም ሲሉ ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል።

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በበኩሉ በአገልግሎት ፈላጊዎች የቀረበው ቅሬታ ትክክል እንደነበር ተናግሮ ቦታው ላይ በሃላፊነት የተቀመጡት ሰው በህመም ምክንያት አገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው እንደሆነ ተናግሮ ነበር።

ይህ አገልግሎት የፊታችን ሰኞ የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም አገልግሎቱ ዳግም ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ከአገልግሎቱ አንገብጋቢነት አንጻር ችግሩ አሁን ላይ መፈታቱን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ነግረውናል፡፡

እንደ አቶ ይግዛው ገለጻ በህመም ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት ሌላ ተወካይ ሰው በማመቻቸት አገልግሎቱ ከትናንት የካቲት 18 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ነው።

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *