የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በህክምና ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በነገው ዕለት ያስመርቃል።

በ1999 ዓ.ም ከተቋቋሙት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎችን በነገው ዕለት ሊያስመርቅ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከዩንቨርሲቲው ሰምቷል።

የዩኒቨርሲቲው የአልሙኒና ቻሪቲ ኦፊሰር አቶ ዘመድኩም ንጉሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በነገው ዕለት 11 ሴትና 21 ወንድ ተማሪዎችን እናስመርቃለን ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በህብረተሰብ ጤና 60 በነርሲንግ 53 በሚድዋይፍ 55 ተማሪዎችን ያስመርቃል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ይገኛሉ ተብሏል።

ዕለቱ የ125 ኛው የአድዋ ድል የሚከበርበት መሆኑ ለተማሪዎቻችን ድርብ ድል ነው ሲሉም አቶ ዘመድኩን ተናግረዋል።

በመቅደላዊት ደረጀ
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *